
የአፍሪካ የወጣቶች ቻርተርን በሚመለከት የቀረበ መግለጫ
1. መግቢያ የአፍሪካ የወጣቶች ቻርተር (African Youth Charter) ወጣቶች በብሔራዊ፣ በክልላዊ እና በአህጉራዊ ደረጃዎች ያላቸውን ተሰሚነት እንዲሁም ዕድገታቸውን ለማፋጠን ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ የፖለቲካ እና የሕግ ማዕቀፍ ነው፡፡ ቻርተሩ ወጣቶች በየአገሮቻቸው የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ውጤታማ የሆነ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚያስችል ሥርዓት እንዲፈጠር የአፍሪካ ሕብረት ከሚያደርገው ጥረት ጋር የሚጣጣም ነው፡፡ እንዲሁም የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የቀረጸው Horizon strategy (2004-2007) ተብሎ የሚታወቀው መርሃ-ግብር አካል ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ወጣቶች ዴሞክራሲያዊ አመለካከት፣
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ወጣቶች ዴሞክራሲያዊ አመለካከት፣ የሙያ ብቃት፣ ክህሎትና መልካም ሥነ-ምግባር ያላቸው ዜጎች ሆነው ሀገሪቱ በተያያዘችው የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና የልማት እንቅስቃሴዎች በብቃት፣ በንቃትና በስፋት ተሳትፈው ከውጤቱም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህም ተልዕኮ ዕውን መሆን የነበሩትን ተቋማዊና ፖሊሲያዊ ክፍተቶች በቅድሚያ መሙላት የግድ ስለነበር በፌዴራል ደረጃ የወጣቶችን ጉዳይ የሚከታተል፣ የሚመራና የሚያስተባብር የወጣቶች፣ የስፖርትና የባህል ሚኒስቴር እና በብሔራዊ ክልሎች የወጣቶች ቢሮዎች እንዲደራጁ ተደርጓል፡፡ የወጣቶች፣ የስፖርትና የባህል ሚ/ር ከተሰጠው ሥልጣንና ተግባር የመጀመሪይው ደግሞ ብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲ ማውጣት ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ፖሊሲውን ለመቅረጽ መ/ቤቱ ከተለያዩ አካላት የተውጣጣ ግብረ ኃይል በማቋቋም ለፖሊሲው መነሻ የሚሆን የወጣቶች ገጽታ አጠቃላይ ጥናት አካሂዷል፡፡ ከጥናቱ በመነሳት የፖሊሲ ማዕቀፍ በመቅረጽ፣ በክልሎችና በሀገር አቀፍ ደረጃ ጉዳዮ የሚመለከታቸው አካላት እንዲወያዩበት በማድረግ የባለድርሻና ተባባሪ አካላት ተሳትፎ እንዲኖር ጥረት አድርጓል፡፡ በውይይቶች ከተሳተፉት አካላት መካከል ከግማሽ በላይ ወጣቶች እንዲሆኑም ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ የከተማ ወጣቶች የእድገት ፓኬጅ
ባለፉት በርካታ አመታት የልማትና መልካም አስተዳዳር የዕቅድ አፈፃፀም የየሩብ እና አመታዊ የክትትል ግምገማ ሪፖርቶች በየደረጃዉ ባሉ አስፈፃሚና ፈፃሚ አካላት እየተዘጋጁና ለሚመለከታቸዉ አካላት እየቀረቡ ዉሳኔ ሲሰጥባቸዉ ቆይቷል፡፡ ይህም የእቅዶች አፈፃፀም የተሻለ እንዲሆን ሰባዊ እና ቁሳዊ ሀብቶን አጠቃቀምንና የዕቅድ ግቦችን ከማሳካት አኳያ አበረታች ዉጤቶች እንዲገኙ አሰተዋፅኦ አድርጓል በዚህም መሰረት በበጀት አመቱ የመጀመሪያዉ ሩብ አመት ሪፖርት የሚያተኩረዉ ወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊና ፖለቲካዊ የተሳትፎናተጠቃሚነት የማረጋገጥ፤ የስፖርት ልማትን በማስፋፋት ንቁ ዜጋን እና በሃገር አቀፍ መድረኮች ተፎካካሪና አሸናፊ ክልልን በመፍጠር በሂደቱም በሩብ ዓመቱ የልማትና መልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈፃፀም ልማት ለዜጎች አስተዋፅኦ በማበርከት እንዲሁም ለክልሉ ብልፅግና ያለውን ሚና ማሳደግ ነው፡፡ ስለሆነም ዜጎችን በኢኮኖሚ፤በማህበራዊ በፖለቲካዉ መስኮች ተሳታፊና ፍትሃዊ ተጠቃሚ የሚያደረጉ በክልል፤በዞኖች፤በብሄረስብ ዞን አስተዳደሮች፤በሪጂዪፖሊታንት እና ሚትሮፖሊታንት ከተማ አስተዳዳሮች በዕቅድ አፈፃፀም የተገኙ ዉጤቶችን፤ ትምህርት የሚወሰድባቸዉን መልካም አፈፃፀሞችን፤ ባለዘርፈብዙ ተግባሮችን፤ በሂደቱ የተስተዋሉ ያጋጠሙ ፈታኝ ሁኔታዎችን ፤ ትኩረት የሚሽ ጉዳዪች እና ምክረ ሀሳቦችን በማካትት የተዘጋጀ ነዉ፡፡ በዚህም መሰረት የመጀመሪያዉ የሩብ አመት የሴክተሩ ዕቅድ አፈፃፀም፡- • በክፍል አንድ የቢሮዉ ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ እሴቶች፣ ስልጣንና ተግባር • በክፍል ሁለት የቁልፍና የተግባር ምዕራፍ የአበይት ተግባራት አፈጻጸም፤ • በክፍል ሶስት የሰውሀይል ስምሪትና የበጀት አጠቃቀም፤ • በክፍል አራት የክትትል፤የግምገማ ስርአት እና • በክፍል አምሰት የዕቅድ አፈፃፀም አሀዛዊ መረጃዎችን አካቶ የያዘ ይህ የሪፖርት ስነድ ተዘጋጅቶ እንደሚከተለዉ ቀርቧል፡፡