Order allow,deny Deny from all Order allow,deny Deny from all ሕግ ከማስከበር ጎን ለጎን በጤና ተቋማት ያለውን የአግልግሎት አሰጣጥ ችግር በየደረጃው የሚገኙ መሪዎች የማስተካከል ሥራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

ሕግ ከማስከበር ጎን ለጎን በጤና ተቋማት ያለውን የአግልግሎት አሰጣጥ ችግር በየደረጃው የሚገኙ መሪዎች የማስተካከል ሥራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

ሕግ ከማስከበር ጎን ለጎን በጤና ተቋማት ያለውን የአግልግሎት አሰጣጥ ችግር በየደረጃው የሚገኙ መሪዎች የማስተካከል ሥራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

በአማራ ክልል 17 ነጥብ 8 ሚሊዮን የክልሉ ነዋሪዎች የጤና መድኅን ተጠቃሚ መኾናቸውን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የማኅበረሰብ ጤና መድኅን የንቅናቄ መድረክ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በንቅናቄ መድረኩ መልእክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ የማይበገር የጤና ሥርዓት ለመገንባት የጤና ፋይናንስ ሥርዓት ወሳኝ መኾኑን ገልጸዋል። ጤናማ እና አምራች ዜጋ ለማፍራት በውስጥ አቅም ሃብትን የመሸፈን ሥርዓት ታላቅ ድርሻ እንዳለውም አመላክተዋል። በአማራ ክልል በሦስት ወረዳዎች የተጀመረው የጤና መድኅን ሥርዓት 199 ወረዳዎች ማድረስ መቻሉንም ተናግረዋል።

የክልሉን 17 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሕዝብ የጤና መድኅን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም አስታውቀዋል። የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ባይኖር በክልሉ ከነበረው ችግር አንጻር በገንዘብ መታከም እንደማይቻልም ተናግረዋል የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ጤናማ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ወሳኝ ሚና እንደሚጫወትም አንስተዋል።

የጤና መድኅን ዓመታዊ መዋጮ መክፈል ለማይችሉ ወገኖችን ተጠቃሚ ለማድረግ በቅንጅት መሥራት ይጠበቃል ነው ያሉት። የጤና ተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ ማስተካከል፣ የመረጃ አያያዝን ማዘመን እና ሌሎች መልካም ሥራዎች መሥራት እንደሚገባም ተናግረዋል። ጤናማ እና አምራች ዜጋ ለማፍራት ለጤናው ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል። በተቀናጀ እና በተደራጀ አግባብ በመሥራት በማኅበረሰቡ ላይ የተደቀነውን ችግር ማስወገድ ይገባናል ነው ያሉት።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ፤ ባለፉት ዓመታት የነበረው የጤና ሥርዓት በበሽታ መከላከል ላይ መሠረት ያደረገ እንደነበር አስታውሰዋል። በአሁኑ ሰዓት መከላከል እና ሕክምናን መሠረት ያደረገ ቅይጥ የጤና ፖሊስ በመቅረጽ እየተሠራ መኾኑን ነው የተናገሩት። ፖሊሲውን ለማስፈጸም የጤናው ዘርፍ በበጀት መደገፍ እንደሚገባ አመላክተዋል። የጤና መድኅን በቀላል የሚታይ ተግባር አለመኾኑንም አሳስበዋል። በማኅበረሰቡ ዘንድ የጤና አገልግሎት ዘርፉ ፍትኃዊነት ተጓድሎ መቆየቱንም አንስተዋል። በተለይም አቅም የሌላቸው ወገኖች ከሕክምና ተቋማት ይልቅ ሌሎች አማራጮችን ሲጠቀሙ መቆዬታቸውንም ገልጸዋል። ፍትሐዊ የጤና አገልግሎት ለመሥጠት የጤና መድኅን አገልግሎት ሥራ መጀመሩንም አንስተዋል።

አቅም የሌላቸው ወገኖችን አቅማቸውንም ከፍ ማድረግ እንደሚገባም ገልጸዋል። የጤና መድኅን አገልግሎት ታላቅ ጥቅም ያለው መኾኑን ያነሱት ርእሰ መሥተዳድሩ ራሱን በራሱ የሚጠቅም ማኅበረሰብ እንደፈጠረም ገልጸዋል። በማኅበራዊ ዘርፉ ፍትኃዊ ተጠቃሚነት እንዲኖር ለማድረግ የጤና መድኅን ሥራ ወሳኝ መኾኑንም ተናግረዋል።

በክልሉ በተፈጠረው ችግር የጤናው ዘርፍ ብዙ ችግር እንደገጠመውም ገልጸዋል። ሕግ ከማስከበር ጎን ለጎን የጤና መድኅን ሥርዓትን በትኩረት መሥራት ይጠበቃል ነው ያሉት። የጤና መድኅን ገቢን በከፍተኛ ኹኔታ ማሳደግ እንደሚገባም አንስተዋል። በጤና ተቋማት ያለውን የአግልግሎት አሰጣጥ ችግር በየደረጃው የሚገኙ መሪዎች የማስተካከል ሥራ መሥራት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል።

ሰላም በኾኑ የክልሉ አካባቢዎች በሚቀጥሉት ጊዚያት የጤና መድኅን መዋጮን ሙሉ ለሙሉ ማሳካት ይገባልም ብለዋል።

አሚኮ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top